ስፓርት

የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን የተማሪዎች  የእግር ኳስ ውድድር  ተጀመረ

By Mikias Ayele

January 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን የተማሪዎች  የእግር ኳስ ውድድር   በአዳማ ከተማ ተጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዋና ፀሃፊ ባህሩ ጥላሁን ÷ የፓን አፍሪካኒዝም ሻምፒዮን   ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አንፃር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው÷መሰል ውድድሮች  ተተኪ ስፖርትኞችን ከማፍራት ባሻገር ክልሎች እርስ በእርሳቸው ግንኙነታቸውን የሚያጠናክሩበት መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በውድድሩ ስድስት የወንድና አራት የሴት የእግር ኳስ ቡድኖች  ተሳታፊ ሲሆኑ÷ ውድድሩን በድል የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ለ2ኛ ጊዜ በታንዛኒያ በሚካሄደው የፓን አፍሪካ ሻምፒዮን ተሳታፊ  እንደሚሆኑ  ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ውድድሩ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል፡፡

በሰላማዊት ተስፋየ