የሀገር ውስጥ ዜና

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ

By Meseret Awoke

January 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስራ ላይ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሲሚንቶ ምርታቸውን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እና የግብአት አቅርቦት ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ዑማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ ውይይቱን ከሲሚንቶ ፋብሪካ ኃላፊዎች እና የክልል ማዕድን ኃላፊዎች ጋር ተካሂዷል።

በቅርቡ ስራ ለመጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ያለው የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በምክክሩ ላይ ተሳትፏል ነው ያሉት፡፡

ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉ የግብአት አቅርቦት እንዲያገኝ መደረጉንም አንስተዋል።

በውይይቱ አዳዲስ ለሚገነቡ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች መደረግ ስላለበት ድጋፍ ማንሳታቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፥ በተለይም ክልሎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!