Fana: At a Speed of Life!

ኮሚቴው በምዕራብ ጉጂ ዞን በጸጥታችግር ለተፈናቀሉ 24 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ በጸጥታ ችግር ለተፈናቀሉ 24 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
 
ኮሚቴው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ ÷በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስቷል፡፡
 
በቅርቡም ኮሚቴው በምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ በአካባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ 24 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማሰራጨቱን አመላክቷል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.