የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምስረታ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

By Mikias Ayele

January 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምስረታ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው የመስራች ጉባኤ አባላት፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት ምስረታ ዋና አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤዎች የሚመረጡ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡