Fana: At a Speed of Life!

የዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝነት ማረጋገጥ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ያስችላል – የትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝነት ማረጋገጥ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቁም በላይ በተቋማቱ የሚነሱ ልዩ ልዩ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስችላል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴዔታ ሳሙዔል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ነጻ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት በነጻነት መስራት ፣ እውቀታቸውን ማካፈል እና የሚጠበቅባቸውን ተግባር መፈጸም አይችሉም፡፡

ለዚህም የትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ በማድረግ በሃገር ግንባታው ላይ የራሳቸውን ሚና መወጣት እንዲችሉ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድም ራስ ገዝነቱ ተቋማዊነታነታቸውን የሚያላብስ በመሆኑ ምን ዓይነት ሰው በምን ዓይነት ክፍያ እንቅጠር ከሚለው ጀምሮ በሃብት አስተዳደር ላይም ጥቅሙ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ተጠያቂነት ያለው በመሆኑ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት ክትትል እንደሚደረግበት የተገለፀው ራስ ገዝነቱ÷ ዩኒቨርሲቲዎች የምዘና እና ስርዓተ ትምህርታቸውንም በነጻነት በማዘጋጀት በሃገር ግንባታው ላይ የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

በሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.