የሀገር ውስጥ ዜና

አፈጉባዔ ታገሠ ጫፎ በቅርቡ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የምርጫ ካርድ ወሰዱ

By ዮሐንስ ደርበው

January 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ ታገሠ ጫፎ በአርባምንጭ ከተማ ሼቻ ቀበሌ ተገኝተው ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የምርጫ ካርድ ወሰዱ ።

አፈ ጉባኤ ታገሰ የምርጫ ካርድ ሲወስዱ እንደገለጹት÷ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የተለያዩ የአደረጃጀት ጥያቄዎች በየምክር ቤቶቻቸው ሲነሱ ቆይተዋል፡፡

እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ መንግስትና ገዥው ፓርቲ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል ማለታቸውን ከጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡም ባሉ ቀሪ ቀናት የምርጫ ካርድ በመውሰድ ይበጀኛል የሚለውን ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በካርዱ ሊወስን ይገባል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!