Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል መንግስት የፀረ ሙስና ኮሚቴ አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ የፀረ ሙስና ኮሜቴ አቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ገረመው ገብረፃድቅ እንዳሉት ÷የክልሉ መንግስት ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ለማስወገድ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴዎች ከሰባት የክልሉ መሥሪያ ቤቶች አዋቅሮ ወደ ሥራ ገብቷል ፡፡
የኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነትም ከዚህ በፊት በጥናት ተለይተው የቀረቡትንና ሌሎች፣ የሙስና ተዋንያንን እየለዩ ለህግ ስለመቅረባቸው መከታተል እና ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ÷የተዘረፉ የህዝብና የመንግስት ሀብቶች እንዲመለሱ ክትትል እንደሚያደርግ እና በሂደቱ የሚሳተፉ ተቋማት በሕግ በተደነገገው መሰረት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን እንደሚከታተልና ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለጹን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.