Fana: At a Speed of Life!

የአራት ዓመት ሕጻንን የደፈረው ግለሰብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳውላ ከተማ በአራት ዓመት ሕጻን ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡

የሳውላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት አስተባባሪ አቶ ሸሪፍ ጂብሪል እንደገለጹት፥ ተጠርጣሪው ወጣት ሕጻኗን ታኅሣሥ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አስገድዶ የመድፈር ወንጀል መፈጸሙ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎች ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑም ግለሰቡ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

የሳውላ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ማስረሻ ሰለሞን÷ ውሳኔው በሕጉ መሰረት ተገቢነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.