በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በተከሰተ የእሣት አደጋ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ገነት ሼዶች ተብሎ በሚጠራው ቦታ በተከሰተ ድንገተኛ የእሣት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡
ከቀኑ 9:40 የተከሰተው ይህ የእሣት አደጋ በስድስት ሼዶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ከክፍለ ከተማው ከሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የእሳት አደጋው ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ÷የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡