Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ስምንት ሆስፒታሎችን ጨምሮ 26 ጤና ጣቢያዎች መሰረታዊ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ስምንት ሆስፒታሎችን ጨምሮ 26 ጤና ጣቢያዎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተነገረ።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባደረጉት ቆይታ፥ ስራ የጀመሩት የጤና ተቋማት ባለፉት ጥቂት ቀናት ከ83 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠታቸውን ተናግረዋል።

መንግስት እና አጋር አካላት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያደረጉበት 225 ሜትሪክ ቶን የጤና ግብአት ወደ ትግራይ ክልል የጤና ተቋማት ተደራሽ መደረጉንም ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹት።

የአምቡላንስ እጥረት እንዳለ የተናገሩት ዶክተር አየለ፥ ችግሩን ለመፍታትም በአጋር አካላት የተገዙ አምቡላንሶች ወደ ክልሉ እንደሚላኩ ጠቅሰዋል።

በክልሉ ያሉ የደም ባንክ እና የኦክስጅን ማምረቻ ማዕከላትን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል።

በዙፋን ካሳሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.