የሀገር ውስጥ ዜና

“ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በሠመራ እየተካሔደ ነው

By Melaku Gedif

January 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው 13ኛው “ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ እየተካሔደ ነው።

ከ1950ዎቹ ጊዜያት አንስቶ በየዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ ሁነቶች፣ በታሪክ አንጓዎች የተከሰቱ የሕዝብ ጥያቄዎች፣ ለሀገር ሉዓዊነት የተከፈሉ መስዋዕትነቶችና ከኢትዮጵያ የልማት ጉዞዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው አንኳር ሀገራዊ ክንውኖችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዕይታ ቀርበዋል።

በዕለቱ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አማካኝነት በአፋርኛ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው አሻራ መጽሃፍ በዕለቱ እንግዶች ተመርቋል።

 

በቅድስት ተስፋዬ