ኮሚሽኑ ህብረተሰቡ የገና በዓልን ሲያከብር ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ አሳሰበ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገና በዓል ሲከበር ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩት በዓላት መካከል ተጠቃሽ የሆነው የገና በዓል የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 29 ቀን ይከበራል።
በመሆኑም በዓሉ ሲከበር በተለይም ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ከሆኑ ነገሮች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማሳሰቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጉልላት ጌታነህ ፥ በዓሉ ሲከበር ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች እንዲጠነቀቅም ነው ያሳሰቡት።
በበዓሉ ወቅት ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በፍጥነት ለመቆጣጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር መዘርጋቱም ተጠቁሟል፡፡
እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በነጻ የስልክ መስመር 939 ፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ 011 156 86 01 ደውሎ ማሳወቅ እንደሚቻል መልዕክት ተላልፏል፡፡