የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገላን ከተማ የሚገኘውን የቢኬ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ከአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ገላን ከተማ ያለው ቢኬ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ ከባድ መኪኖችን፣ አውቶብሶችን በመገጣጠም እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማምረት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ’’ኢትዮጵያ ታምርት’’ ንቅናቄ ተሳተፉ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

By Melaku Gedif

January 04, 2023

በኢትዮጵያ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገላን ከተማ የሚገኘውን የቢኬ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ ከአዲስ አበባ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ገላን ከተማ ያለው ቢኬ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ ከባድ መኪኖችን፣ አውቶብሶችን በመገጣጠም እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማምረት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች  እየተስፋፉ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ’’ኢትዮጵያ ታምርት’’ ንቅናቄ ተሳተፉ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡