የሀገር ውስጥ ዜና

የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Alemayehu Geremew

January 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሠ-መሥተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ ምክትል ርዕሠ-መሥተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ፣በዘርፉ የተሰማሩ ባለሐብቶችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ከባለሐብቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል