ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሆራ ኢንዱስትሪን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በገላን ከተማ የሆራ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ዛሬ በገላን ከተማ የ’’ኢትዮጵያ ታምርት’’ ሁለተኛው ጉብኝት በሆራ ኢንዱስትሪ ማድረጋቸውን አስፍረዋል፡፡
በዚህ ኢንዱስትሪ ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ ፣ መቁያ እና ሲሚንቶ ማሸጊያ ማምረቻ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለፁት።
ኢንዱስትሪ ማሳዳግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ትልቅ ሚና እንዳለውም አስፍረዋል ::
በድጋሚ በ’’ኢትዮጵያ ታምርት’’ ተሳታፊ እንሁን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡