Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በቀን ከ280ሺህ በላይ እንጀራ የሚጋግር የእንጀራ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከ280ሺህ በላይ እንጀራ የሚጋግር 4ሺህ ለሚደርሱ እናቶችና ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር የእንጀራ ፋብሪካ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ እናቶቻችን እጃቸው እስኪሻክር የሚለፉበት እንጀራ አሁን የገቢ ምንጭ ይሆናቸው ዘንድ እነሆ ዛሬ ይህ 1ሺህ ምጣድ የሚኖረው የእንጀራ ፋብሪካ በ3 ወር ውስጥ ተገንብቶ ወደ ስራ ይገባል።

የ”ሌማት ትሩፋት” ብለን ስራ ስንጀምር እኛ ኢትዮጵያውያን ሌማታችን ያለ እንጀራ ሌማት ሊሆን አይችልም ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

በዚህም የገበታው መሰረት የሆነውን እንጀራ እንደ ልብ እንዲቀርብ የሚያግዝ በሃገራችን ደረጃ በዓይነቱ ልዮ የሆነውን ፋብሪካ ከልማት አጋሮቻችን ጋር በመሆን ስራውን አስጀምረናልም ነው ያሉት፡፡

ከጎናችን ለሆኑት የኦቪድ ግሩፕና የታፕ ፉድ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.