Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በሦሥት የእሳት አደጋዎች 90 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሾላ ገበያ ፣ በአቃቂና ሌሎች ስፍራዎች በደረሰ የእሳት አደጋ 90 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በሾላ ገበያ፣ አቃቂ እና በዮሴፍ አካባቢዎች በዚህ ሳምንት የደረሱ የእሳት አደጋዎች ከዚህ በላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ባለሙያዎች ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ይክፈለው ወልደመስቀል ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ከገና እና ጥምቀት ጋር ተያይዞ የእሳት አደጋ እንዳይደርስ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ዋና ኮሚሽነሩ ፍሰሃ ጋረደው አሳስበዋል፡፡

የእሳትና ሌሎች አደጋዎች ከደረሱም የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ ለመቆጣጠር 900 ባለሙያዎችና 70 የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች ዝግጅት ማድረጋቸውንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ለእሳት አደጋ ዋነኛ ምክንያት የኤሌክትሪክ እና በቤት ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ ነገሮች በመሆናቸው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም ኃላፊዎቹ አሳስበዋል፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.