Fana: At a Speed of Life!

አንበሳ ባንክ በግጭት ምክንያት አግልግሎት ተቋርጦባቸው በነበሩ  የተለያዩ ከተሞች ዳግም ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንበሳ ባንክ በግጭት ምክንያት አግልግሎት ተቋርጦባቸው በነበሩ ሰባት የተለያዩ ከተሞች ዳግም ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የአንበሳ ባንክ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር ሙሉጌታ ተክሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በዛሬው ዕለት በመቀሌ፣ አክሱም፣ ዓድዋ፣ ሽረ፣ አላማጣ፣ ኮረም እና ዋጃ ከተሞች የሚገኙ ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡

በእነዚሁ ቅርንጫፎች÷ ገንዘብ መላክ፣ መቀበል እንዲሁም ክፍያ መፈጸም እና የሃዋላ አገልግሎት መጀመሩን አቶ ሙሉጌታ አረጋግጠዋል፡፡

አገልግሎቱ በተቋረጠባቸው ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ቅርንጫፎችን ዳግም ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.