Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ልትመለስ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ ጥር 15 በሚካሄደው 22ኛው የአራምኮ ሂዩስተን የግማሽ ማራቶን ውድድር የርቀቱ የምንጊዜም ታላቅ ሯጮች መካከል አንዷ የሆነችው ጥሩነሽ ዲባባ ትሳተፋለች፡፡
የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ እና የአምስት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊዋ አትሌት ጥሩነሸ ዲባባ በግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ የግሏ ፈጣን ሰዓት አላት፡፡
በሂውስተን ግማሽ ማራቶንም÷ በርቀቱ 1 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ያላት አሜሪካዊቷ ኤምሊ ሲሰን እና 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ ያላት ኢትዮጵያዊቷ ሕይወት ገ/ኪዳን የጥሩነሽ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.