Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ለ21 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ ለ21 አቅመ ደካሞች ባለ ሦስት ወለል የመኖሪያ ሕንጻ አስረከቡ።

በከተማ አስተዳደሩ መንገዶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለበዓል መዋያ የሚሆን በግ፣ ዶሮ እና ዘይትን ጨምሮ ሌሎች ሥጦታዎችን ከንቲባ አዳነች ለአቅመ ደካሞች አስረክበዋል።

እንዲሁም ለአምስት አርቲስቶች በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ባለሀብቶችን በማስተባበር የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶችን አስረክበዋል።

ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ፥ ከሀገር እና ትውልድ ባለውለታዎች፣ ከአቅመ ደካሞች ጎን መቆም ይገባል ብለዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ አካባቢዎቸ የተገነቡ 197 ቤቶችን በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ለነበሩ፣ ለሀገር ውለታ ለዋሉ አርቲስቶችና ጀግኖች አስረክበዋል።

ቤት የተበረከተላቸው የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች÷ የዜማና ግጥም ደራሲ ይልማ ገብረአብ፣ ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ፣ ድምፃዊ አሸናፊ ከበደ፣ ድምጻዊ ሻምበል በላይነህ እና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የሬዲዮና ቴሌቪዥን ድራማ ደራሲው መስፍን ጌታቸው ወላጅ እናት ወይዘሮ ሎሚናት ገብረመስቀል መሆናቸው ተገልጿል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.