የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ጋር በስልክ ተወያዩ

By Feven Bishaw

April 03, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የኮቪድ-19 ሥርጭት ለሚያስከትላቸው ፈታኝ ሁኔታዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል የጋራ አመራር ላይ ነው ፕሬዚዳንት ካጋሜ ጋር በስልክ የተወያዩት።

በውይይታቸው ላይም አፍሪካ ከቀውሱ በኋላ ሊያጋጥማት የሚችለውን የኢኮኖሚ መሰናክል ለመቋቋም የጋራ ጥረት እጅግ ያስፈልጋል ብለዋል በውይይታቸው።