Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ላይ ማሻሻያ ልታደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ለውጭ ሃይሎች ተጽዕኖ ሳትንበረከክ ብሄራዊ ጥቅሟን ታስከብራለች ሲሉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ተናገሩ፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት ኔታንያሁ በቅርቡ አዲስ መንግስት መስርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ  በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ÷ እስራኤል ከዚህ ቀደም በነበራት  የውጭ  ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ማሻሻያ እንደምታደርግ  አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይ የሚወጣው የሀገሪቱ  የውጭ ጉዳይ ፖሊስም  የእስራኤልን ሉዓላዊነት እና ብሄራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ መሆኑ ነው ያብራሩት፡፡

ለዓለም አቀፍ ጫናዎች አንበረከክም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የእስራኤልን ግዛት ለማስከበር እና ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ ለመዝለቅ በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ከውጭ ሀገራት ጋር የሚኖረው ሁለንተናዊ ግንኙነትም የጋራ ጥቅምን ባስከበረ መልኩ እንደሚሆን አጽንኦት  መስጠታቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.