Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ታዳጊ ዳግማዊ የኳስ ችሎታውን እንዲያዳብር ድጋፍ ልናደርግለት ይገባል አሉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ታዳጊ ዳግማዊ ቴዎድሮስ የኳስ ችሎታውን እንዲያዳብር ድጋፍ ልናደርግለት ይገባል አሉ፡፡
ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ የ12 ዓመቱ ታዳጊ ዳግማዊ ቴዎድሮስን ከአባቱ ቴዎድሮስ ባጫ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ታዳጊው ከሕጻንነቱ ጀምሮ የኳስ ችሎታውን እያዳበረ እና ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ህልሙ እንዲሳካም ከአባቱ ጋር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።
ከአራት ዓመታት በፊት ሩሲያ ዘንድሮ ደግሞ ኳታር ባስተናገዱት የዓለም ዋንጫ÷ አባትና ልጅ በክብር እንግድነት በፊፋ ግብዣ በመርሐ ግብሮቹ ላይ መገኘታቸው ይታወቃል፡፡
ዳግማዊ ኳስ በማንጠባጠብ የሁለት ብር ቻሌንጅ አስጀምሮ በዚህ ችሎታው ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ከፍተኛ ገንዘብ ማሰባሰቡ ተገልጿል፡፡
ታዳጊው ሳያቋርጥ እስከ 974 ድረስ ኳስ በእግሩ የማንጠባጠብ ልዩ ችሎታ እንዳለው ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ የታዳጊው የእግር ኳስ ችሎታ የበለጠ እንዲዳብር አበረታተው÷ ራዕዩ እንዲሳካ የእግር ኳስ አካዳሚ መግባት ዋነኛው አማራጭ በመሆኑ እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የሚችሉ ሁሉ እዲደግፉ ጠይቀዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.