Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ሥር በሚገኙ ሥድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት አደረገ፡፡

በስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 እስከ ታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያካሄድ የነበረው የመራጮች ምዝገባ ተጠናቋል፡፡

ይህን ተከትሎም የመራጮችን መዝገብ ለአምስት ቀናት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት መደረጉን ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቦርዱ እስከ ጥር 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ የመራጮችን መዝገብ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት እንደመሆን አስታውቋል።

የተጠናቀቀው የመራጮች ምዝገባ፥ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ የመራጮች ምዝገባው በተሠረዘባቸውና በቦርዱ ውሣኔ በድጋሜ ከታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. (ታኅሣሥ 29 ሳይጨምር) እስከ ጥር 1 የመራጮች ምዝገባ የሚካሄድባቸውን ምርጫ ጣቢያዎች እንደማይጨምርም ነው ያስታወቀው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.