Fana: At a Speed of Life!

ከ300 ለሚበልጡ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ከ300 በላይ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና መስጠቱን ገለጸ።

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የ2022 የሥራ ዘመን በልብ ማዕከል ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም በልብ ማዕከሉ ለ8 ሺህ 674 ሕሙማን የልብ ሕክምና ክትትል እንዲሁም ለ328 ሕሙማን የልብ ቀዶ ሕክምና እና በደም ስር በኩል የሚከናወን የልብ ሕክምና አገልግሎት በነፃ ለመስጠት መቻሉ ተገልጿል፡፡

በልብ ማዕከል ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ከ7 ሸህ 400 በላይ ሕሙማን ወረፋ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሚክሎል መንግስቱ እንዳሉት፥ ይህ ቁጥር ከማዕከሉ የመስራት አቅም እና ወረፋ ከሚጠብቁ ሕሙማን ቁጥር አንፃር እጅግ አነስተኛ አገልግሎት ቢሆንም ከሕብረተሰቡ እና ከተለያዩ ተቋማት በተገኘው ድጋፍ አገልግሎቱን ማስቀጠል መቻሉን ከማዕከሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የድርጅቱ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አርቲስት መሠረት መብራቴ፣ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳላሃዲን ከሊፋና የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሕክምና ካገኙ ሕፃናትና ወላጆች ጋር በጋራ በመሆን ድጋፍ ላደረጉ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት ለሚገኙ ግለሰቦች እንዲሁም የግልና የመንግስት ተቋማት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ማዕከሉን በ6710 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ላይ “OK” ብሎ በመላክ ህብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.