Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ አካሔዱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በማዘጋጃ ቤት አካባቢየፅዳት ዘመቻ አካሔዱ፡፡

የጽዳት ዘመቻ የተካሔደው÷ ወደ አትክልት ተራ ፣ መሃሙድ ሙዚቃ ቤት እና ቸርችል ጎዳና በሚወስዱ መንገዶች በሦስት አቅጣጫዎች ተከፍሎ ነው፡፡

የፅዳት ዘመቻው÷ ከተማችን በአብሮነት ትፀዳለች !፣ በትብብር ትገነባለች !፣ በፍቅር ትለመልማለች ! በሚል መሪ ሐሳብ ነው የተከናወነው፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር÷ ከተማችን ሁሉን አቅፋ የምትኖር፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ሶስተኛዋ የዲፕሎማቲክ ከተማ ናት ብለዋል፡፡

ልክ እነደ ስሟ ውብ፣ ፅዱ እና ሰላማዊ ለማድረግ ሁላችንም በዚህ ጥረት ውስጥ መሳተፍ እና መትጋት ያስፈልገናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በከተማችን ለአይን ከሚታይ ቆሻሻ ባለፈ፣ የማይታየውን ከፋፋይ ሀሳብ ማፅዳት እና መንቀል እንደሚያስፈልግም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በጽዳት ዘመቻው ላይ የሐይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የከተማዋ የካቢኔ አባላት፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች፣ አምባሳደሮች፣ የውጭ ሀገራት ኩባንያዎች ተወካዮች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ ተማሪዎችና መምህራን፣ የፅዳት አንባሳደሮች፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አባላት እና በከተማዋ በየደረጃው ያሉ የወጣት አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.