Fana: At a Speed of Life!

የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና መንግስታት ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና መንግስታት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ፣ የጋምቤላ ከልል ርዕሰ መስተዳደር ኡሞድ ኡጁሉ፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መልዕክት÷ በዓሉን ስናከብር ርስበርስ በመዋደድና በመፈቃቀር፣ ቂመኝነትንና ተንኮልን ከልባችን በማስወገድ ወንድማማችነትን በሚያጠናከር መልኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ርስቱ ይርዳ÷ ያገኘነውን የሰላም ዕድል በመጠቀም የሕዝባችንን የመልማት እና የማደግ ፍላጎት ለማሳካት በትኩረት የምንሠራበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት÷ የገና በዓል የእምነቱ ተከታዮች መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት፣ ተቻችለውና ተከባብረው በጋራ መኖርንና መሥራትን ለመላው የዓለም ሕዝብ የሚያሳዩበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል፡፡

የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ባስተላለፈው መልዕክት÷ ሕዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም በተለመደው የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህል እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ባስተላለፈው መልዕክት÷ የሐይማኖቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ አንድነትና አብሮነትን የሚያጠናክሩ ተግባራት በመፈጸም ሊሆን ይገባል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክት÷ ይህን የፍቅርና የምህረት በዓል ስናከብር እንደ ሕዝብ አንዳችን ለሌላችን ይቅር በመባባልና በፍቅር እንዲሁም በመተሳሰብና በመተጋገዝ መሆን እንዳለበት ማስታወስ ይገባናል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.