Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተሾመ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከታኅሣሥ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ፡፡

አምባሳደር ተሾመ ከዚህ ቀደም በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል፡፡

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በተደራጀ ኃይል ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ አልሞ የተቋቋመ ነው፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲሳተፉ ለማስቻል የኮሚሽኑ አስፈላጊነት ተመላክቷል፡፡

ይህን ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሕዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 15 መደበኛ ስብሰባ በማጽደቅ እና ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮም በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.