Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር አህመዲን መሃመድ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ድርጅትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሃመድና የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ድርጅቶች አመራሮች የመከላከያ ኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የኮንስትራክሽን ግብዓት ምርት ሒደትንና የማስፋፊያ ሥራዎችን፣ የብረት ሥራዎችን እንዲሁም የተለያዩ የእንጨት ሥራ ሒደትና ውጤቶችን መመልከታቸውን ዶ/ር አህመዲን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
ምርታማነትንና ጥራትን ለማሻሻል እየተካሄዱ ያሉ የቴክኖሎጂና ማሽነሪ ማሻሻያዎች በቀጣይ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የራሱን አስተዋፅኦ ሊያደርግ በሚችልበት አቅም ላይ ለመድረስ ድርጅቱ እያካሄዳቸው የሚገኙ ሪፎርሞች አካል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
 
አመራሮቹ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ ድርጅት እና የዘርፍ ሥራ አመራርን በተለይም የኢንተርፕራይዝ ቁመና ያለው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ግሩፕ ግንባታ አንፃር ያለውን የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀምም ገምግመዋል፡፡
 
በዚህም የኮንስትራክሽን ዲዛይን ሥራዎች ጥራት፣ የመንገድና ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ማምረቻ አፈፃፀም እና የድርጅቶችን የፋይናንስ ጤናማነት ከማረጋገጥ አኳያ ያሉ መሻሻሎችን እንዲሁም ክፍተቶችን መለየታቸው ተጠቁሟል፡፡
 
በቀጣይም ድርጅቶች የያዟቸውን ተቋማዊና ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ሊያጠናቅቁ ስለሚችሉበት ሁኔታ በመምከር በቅንጅትና ቁርጠኝነት መከናወን በሚቻልባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸው ተጠቁሟል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.