Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ ።
 
ስምምነቱን የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ግዛው እና ኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ማህበር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብዲ ዘነበ ተፈራርመዋል።
 
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በባር ዘርፍ ልማት፣ ሃብት አስተዳደር፣ በእውቀት ሽግግር እንዲሁም በንግድ ትብብር ተቀናጅተው በመስራት ሀገራዊ የባቡር መስመሩን ውጤታማ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል።
 
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ÷ ስምምነቱ የባቡር ዘርፉን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ዘርፍን በማነቃቃትና በማሳደግ አገርን በጋራ ማገልገል የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።
 
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ምክትል ሰራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ግዛው በበኩላቸው÷ስምምነቱ ዘርፍን ሊለውጡ የሚችሉ ስራዎችን ለማከናወን እንደሚያግዝ ገልጸው በቀጣይ በሌሎች ዘርፎችም በትብብ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.