Fana: At a Speed of Life!

የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተሠራ  መሆኑን አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን  የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

የሐረሪ ክልል የካቢኔ አባላት ዘመናዊ የቄራ አገልግሎት ማዕከል፣ የባህል ማዕከል፣ ሼዶችና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ ተጠናቀው ወደ ሥራ ያልገቡ ፕሮጀክቶች ሥራ እንዲጀምሩ ማስቻል የክልሉ መንግስት  የትኩረት አቅጣጫ  ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ  እንደሚገኙ ጠቁመው÷ የሚከናወኑ ተግባራት የሥራ  ዕድል ፈጠራን የሚያጎለብቱ፣ ገቢ የሚያስገኙ እና  ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ ይሠራል  ማታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.