Fana: At a Speed of Life!

ለ2015/16 የምርት ዘመን 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2015/16 የምርት ዘመን 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈጸሙን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የግብርና ኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ከ12 ነጥብ 8 ሚሊየኑ የአፈር ማዳበሪያ መካከል 5 መቶ ሺህ ኩንታሉ ዩሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

እስካሁን 42 ሺህ ሜትሪክ ቶን ያህሉ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱንም ጠቁመዋል፡፡የሽያጭ ዋጋውን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ዋጋውን መሰረት አድርጎ እንደሚከናወን አመላክተዋል፡፡

የዚህ ዓመት የሽያጭ ዋጋን በተመለከተም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እንዲጠቀም ግብርና ሚኒስቴር ክትትል ያደርጋል ብለዋል፡፡

በይስማው አደራው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.