የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

By Meseret Awoke

January 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ አረጋውያን ፣ አካል ጉዳተኞች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር የገናን በዓል አሳልፈዋል።

በመርሐ ግብሩ 150 ሰዎች ተገኝተዋል።

በአልዓዛር ታደለ