Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም የተለያዩ ሀገራት ዛሬ ገናን በድምቀት አክብረዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢትዮጵያ ውጭ በመላው ዓለም ያሉ የክርስትና እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት (ገና) በዓልን በድምቀት አክብረዋል፡፡

ቢቢሲ ስለኢትዮጵያ ገና አከባበር እንዳለው ፥ በተለይም በላሊበላ በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በገና ዋዜማ እና በዕለቱ በካህናት የተመራ ደማቅ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች አብዛኞቹ የጁሊያን አቆጣጠርን በመከተል የገናን በዓል የሚያከብሩት በፈረንጆቹ ጥር 7 ቀን ነው።

ሁለቱ ብዛት ያለው የእምነቱ ተከታይ ያላቸው ሀገራት÷ ሩሲያ እና ዩክሬን ፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ትልቁ የተባለውን ጦርነት እንደቀጠሉ ቢሆንም በዓለም ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት ገናን እያከበሩ እንደሚገኙ የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

አብዛኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በምስራቅ አውሮፓ የሚገኙ ሲሆኑ ፥ በመላው ዓለም የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በብዛት የሚገኙበት የመካከለኛው ምስራቅን ጨምሮ – በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዚሁ ሣምንት የገናን በዓል ለማክበር ሲባል ፕሬዚዳንት ፑቲን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ ቢያቀርቡም ዩክሬን ጥሪውን ውድቅ ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.