የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች የገና በዓልን በምገባ ማዕከል ከሚገኙ ወገኖችጋር አሳለፉ

By Feven Bishaw

January 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የገና በዓልን በምገባ ማዕከል ከሚገኙ ወገኖች ጋር አሳልፈዋል፡፡

ከንቲባዋ በመዲናዋ ከሚገኙ ምገባ ማዕከሎች አንዱ በሆነው አሙዲ የምገባ ማዕከል ነው ከከረዮ- ጌጃ ሰፈር ወገኖች ጋር በዓሉን ያሳለፉት ፡፡

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ወገኖቻችንን በመመገብ እየተጋችሁ ያላችሁ በጎ አድራጊዎች ፣ አመራሮችና እናቶች ከልባችን እናመሰግናለን “ብለዋል፡፡

በዓሉ የይቅርታ ፣ የአብሮነት፣ የደስታ ፣ያማረና የሰላም እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡