የሀገር ውስጥ ዜና

1ሺህ 17 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

By Feven Bishaw

January 07, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 17 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ዜጎች በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡