Fana: At a Speed of Life!

የሃላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ‘ሴራ’ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው ።

በዓሉ “ሴራችን ተከባብሮ የመኖር ድንቅ ባህላችን” በሚል መሪ ቃል ነው  እየተከበረ የሚገኘው፡፡

የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ልማት መምሪያሃላፊ አቶ ሱልጣን ሁሴን እንደገለፁት÷ የዘንድሮው የዘመን መለወጫ ‘ሴራ’ ወይም ‘መንገሳ’ በዓል ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይከበራል።

በዓሉ የብሔረሰቡ ‘ሴራ’ ባህል አጠቃላይ ህግና ሥርዓቶች ሳይባረዙ ተጠብቀው ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ ሚና እንዳለው መናገራቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ብሄረሰቡ ባህሉን፣ታሪኩንና ቋንቋው በመንከባከብ ጠብቆ በማቆየት ለቀጣዩ ትውልድ ከማስተላለፍም ባሻገር የሰላም፣የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ድሎችን ማጠናከር እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.