Fana: At a Speed of Life!

“የጥርን በባሕር ዳር“ ዝግጅት አካል የሆነው 2ኛው ዓመታዊ የብስክሌት ፌስቲቫል ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የጥር ወርን በባሕርዳር” ዝግጅት አካል የሆነው ሁለተኛው ዓመታዊ የብስክሌት ፌስቲቫል ተካሄደ።

የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ ÷በባሕርዳር ከብክለት ጸፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳደግ የከተማዋ የጥንት መገለጫ የሆነውን የብስክሌት ተጠቀሚዎችን ቁጥር የማሳደግና ለዚህም መንገዶችን ምቹ የማድረግ ስራ በቁርተኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ጭስ አልባ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር የመመካከር ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ገልፀዋል።

ወደ ባሕርዳር የገቡ እንግዶችን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማዝናናት ፣እየገቡ የሚገኙትንና ገና ሊገቡ የሚችሉት ቱሪስቶች በጉጉት እንዲታደሙ ሊገፋፉ የሚችሉ ዝግጅቶችን በማድረግ በኩል ወደ ፊትም በቀሪ የጥር ወር ጊዜያት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ፌስቲቫሉ ለከተዋማ ሁለንተናዊ ዕድገት ፣ለማህበረሰቡ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው መጠቆማቸውንም የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በመርሐ ግብሩ የባሕርዳር ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ፣ በርካታ ብስክሌተኞች ፣ ሌሎች ተሳታፊ የከተማዋ ነዋሪዎችና እንግዶች ተሳትፈዋል።

ጥር ወርን በባሕርዳር የልዩ ልዩ ትዕይንቶች ማከናወኛ በማድረግ የቱሪዝም ፍሰት እንዲሻሻል ፣የከተማዋ ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲጎለብት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.