Fana: At a Speed of Life!

አማኑኤል ኢሳያስ ኢንተርናሽናል የቮሊቦል ኢንስትራክተር ደረጃን አገኘ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ለአማኑኤል ኢሳያስ ኢንተርናሽናል የቮሊቦል ኢንስትራክተርነት ደረጃን ሰጠ።

በዚህም ከአንጋፋው ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ ቀጥሎ አማኑኤል ኢሳያስ ሁለተኛው ኢትዮጵያውያዊ ሆኗል፡፡

አማኑኤል በአሁኑ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃ የቮሊቦል አሰልጣኝነት የምስክር ወረቀት ያለው ብቸኛ ኢትዮጵያዊ አሰልጣኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተጫዋችነት ዘመኑ በሀገር ውስጥ ብቻ ያልተገደበው አማኑኤል÷ ለታንዛኒያው ቲፐር ክለብ ለአምስት ዓመታት በፕሮፌሽናልነት ተጫውቷል።

የታንዛኒያውን ቲፐር እና ሜትሮ ክለቦች እንዲሁም የታንዛኒያ ብሔራዊ ቮሊቦል ቡድን ማሰልጠኑ ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት ወላይታ ዲቻን በዋና አሰልጣኝነት እየመራ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አሰልጣኝ አማኑኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ ከደረጃ 1 እስከ 3 ያሉ ስልጠናዎችን ከማጠናቀቁ በተጨማሪ የተለያዩ ስፔሻላይዜሽን ስልጠናዎች ተከታትሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.