Fana: At a Speed of Life!

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  በጉብኝታቸው ወቅት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከውይይቱ በተጨማሪ ሚኒስትሩ በቻይና መንግስት ድጋፍ የተገነባውን የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና እና መከላከያ  ማዕከል እንደሚጎበኙ ተመላክቷል፡፡

ማዕከሉ በደቡብ አዲስ አበባ የአፍሪካ መንድር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገነባ ሲሆን 90 ሺህ ሜትር ስኩዌር አጠቃላይ ስፋት አለው፡፡

ማዕከሉ ግንባታው ሲጠናቀቅ  የድንገተኛ አደጋ ኦፕሬሽን ማዕከል፣ የመረጃ ማዕከል፣ የላቦራቶሪ፣ የስልጠና ማዕከል፣ የኮንፈረንስ ማእከል፣ ቢሮዎች እና አፓርታማዎችን ይኖሩታል ነው የተባለው፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ በህክምና መሳሪያዎች ከተሟሉ ማዕከላት አንዱ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ይህም በአህጉሪቱ በሽታን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሏል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ቻይና በ2020 የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ዋና መስሪያ ቤት ለመገንባት ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ የተፈፀመ መሆኑን ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.