የሀገር ውስጥ ዜና

8 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

By Feven Bishaw

April 03, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 8 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በተደረገው የድጋፍ ጥሪ መሰረት ዛሬ አልሳም ግሩፕ፣ አምደሁን ጀኔራል ትሬዲንግ እና አቶ ጀማል አህመድ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በጋራ ድጋፍ አድርገዋል።

ድርጅቶቹ በመስቀል አደባባይ በመገኘት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ሃላፊ እና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ አለምጸሀይ ጳውሎስ አስረክበዋል።

4 ሺህ ኩንታል ስንዴ እና በቆሎ፣ 900 ካርቶን የአትክልት ቅቤ እና 2 ሺህ ካርቶን የገላ ሳሙና እንደሚገኙበት ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡