ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ላለፈ ዜጎች ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች

By Tibebu Kebede

April 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለህልፈት ለተዳረጉ ዜጎች እና የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ሂደት ህይወታቸው ላለፈ የህክምና ባለሙያዎች ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጃለች።

በዚህ መሰረት በነገው ዕለት በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ በመላ ሀገሪቱ እና በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ ኤምባሲዎቿ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።

ከዚህ ባለፈም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ስራ ያቆማሉም ነው የተባለው።

በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር 10 ሰዓት ላይም በቫይረሱ ምክንያት ህይዎታቸውን ላጡ ዜጎች በሀገር አቀፍ ደረጃ የሶስት ደቂቃ የህሊና ፀሎት ይደረጋል።

በአሁኑ ወቅት በቻይና በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 81 ሺህ 620 የደረሰ ሲሆን፥ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር ደግሞ 3 ሺህ 322 ደርሷል።

ምንጭ፦ ሺንዋ