ቢዝነስ

ሀገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር በሐዋሳ ሊካሄድ ነው

By Meseret Awoke

January 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር በሐዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ “በሀገሬ ምርት እኮራለሁ፤ ከአገር ውስጥ አምራቾች እገዛለሁ” በሚል መሪ ቃል ከጥር 4 እስከ 9 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል።

በኢንተርፕራይዞች መካከል የእርስ በእርስ የሥራ ትብብር ግንኙነት መፍጠር፣ የገበያ ትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማመቻቸት የባዛርና ኤግዚቢሽኑ ዓላማዎች እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡