Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የጤና መድህን ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀረሪ ክልል “ጥር ወር የጤና መድህን ወር” በሚል መሪ ቃል ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን  የአባላት እድሳትና ምዝገባ ማስጀመሪያ ንቅናቄ ተጀምሯል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ  በንቅናቄው እንደተናገሩት÷ በክልሉ ባለፈው አመት የጤና መድህን የንቅናቄ  ስራ ስኬታማ ነበር፡፡

ለአንድ ወር በሚቆየው ንቅናቄ የአባላቶችን ቁጥር ለማብዛት እና የጤና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በሀረሪ ክልል በ2014ዓ.ም ከ45 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን የማህረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ  ማድረግ የተቻለ ሲሆን÷ በዚህ ዓመትም የአገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡

በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.