የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር ፋርዶዋስ ኦስማን ኤጋል ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሯ እና የልዑክ ቡድናቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ አቀባባል አድርገውላቸዋል፡፡
ልዑካኑ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሲቪል አቪዬሽን መስክ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ እንደሚምከሩ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡