ፓርኩን የበለጠ ለማልማት እየሰራ መሆኑን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክን የበለጠ በማልማት ባለሃብቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ አስታወቀ፡፡
የፓርኩ ስራ አስኪያጅ ጥሩየ ቁሜ እንዳሉት÷ የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ3ኛ ወገን ነፃ ሆኖ ከተረከበው 150 ሄክታር መሬት ውስጥ 75 ሄክታር መሬቱን በማልማት ወደ ስራ ገብቷል።
በፓርኩ ውስጥ ስምንት ሼዶች ተገንብተው በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ለተሰማሩ ኩባንያዎች ክፍት መደርጉን አውስተዋል።
ፓርኩ የጉምሩክ፣የባንክና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጥ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ምርታቸውን ወደ ውጭ ለሚልኩ ኩባንያዎች ምቹ ሁኔታ ያለው መሆኑን ገልፀዋል።
“አንበሳ ኢሊት ታክቲካል ቴክስታይል ኢንዱስትሪ” የተባለ የእስራኤል ኩባንያም በፓርኩ ውስጥ ማልማት የሚያስችለውን የሼድ ርክክብ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡