ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና በታይዋን አቅራቢያ ተጨማሪ ወታደራዊ ልምምድ አካሄደች

By Alemayehu Geremew

January 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ወታደራዊ ልምምዶችን በታይዋን አቅራቢያ ማካሄዷን አስታውቃለች፡፡

ቤጂንግ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የአሁኑን ጨምሮ ሁለት ወታደራዊ ልምምዶችን በታይዋን አቅራቢያ ማካሄዷ ተገልጿል፡፡

ልምምዶቹ የሀገሪቷን የዓየር ፣ የምድር እና የባሕር ኃይሎች ብቃት ለመፈተሽ የተካሄዱ መሆናቸውን የቻይና ምሥራቃዊ ዕዝ ጦር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሺ ዪ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ጥምር ልምምዶቹ ሌሎች የውጭ ኃይሎችና የታይዋን ተገንጣዮች ለሚቃጡት ግጭት ቀስቃሽ እርምጃ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ለማስተላለፍ ያለመ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የታይዋን ፕሬዚዳንት ጽኅፈት ቤት በበኩሉ÷ ድርጊቱን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ሲል ማጣጣሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡