ሾልኣ -ካሻ የባስኬት ብሔረሰብ ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባስኬት ብሔረሰብ በዓመት አንድ ጊዜ የሚከበር ሾልኣ- ካሻ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ላስካ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡
ሾልኣ-ካሻ ህብረተሰቡ ሰላምና ብልጽግናን የሚጠይቁበትና የሚያመሰግንበት ሥርዓት ነው ።
ይህ ሰርዓት የሚካሄደው በዓመቱ የእህል ምርት ከደረሰና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ምርት ከሰበሰቡ በኋላ የሚከበር ነው ።
በዚህም የጎሳ መሪ “ካቲ” የደረሰውን እህል ካልባረኩና ካልቀመሱ ድርቅን መሰል አደጋ ያመጣል ተብሎም ይታመናል ።
የካሻ ሰርዓት ሲከናወን የባስኬት ብሔረሰብ ሀገር በቀል ዛፎችን በመንከባከብና ደንን በመጠበቅ ስለሚከበር በብሔረሰቡ ዘንድ ትልቅ ባህላዊ እሴት ያለው ባህል ነው ።
የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታመነ ታምርሶ እንደገለጹት፥ በባስኬት ብሔረሰብ ዘንድ እንደ ዘመን መለወጫ የሚከበረው ሾልኣ-ካሻ በዓል አንድነትና ሰላምን ከማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
ይህ በዓል በዋናነት አካባቢን መጠበቅ ላይ ትኩረት ስለሚያደርግ በዓመቱ ከ10 ወራት በላይ ባስኬቶ ዝናብ ያገኛል።
በዓሉ ዛሬ በፓናል ውይይት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን ፥ በነገው ዕለት በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚቀጥልም ነው የተገለጸው።
በመርሃ ገብሩ የኢፌዴሪ ብዝኃ-ህይወት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ፈለቀ ወልደየስን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል ።
በማቴዎስ ፈለቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!