Fana: At a Speed of Life!

ጋሬዝ ቤል ከእግር ኳስ ሕይወትራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል ጋሬዝ ቤል ራሱን ከክለብና ከብሄራዊ ቡድን ማግለሉን አስታውቋል፡፡
ቤል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ÷ “የምወደውን የእግር ኳስ ስፖርት የመጫወት ህልሜን በማሳካቴ እድለኛ ነኝ ፤ነገር ግን ከዚህ በላይ በእግር ኳስ ሕይወት አልቀጥልም ብሏል፡፡”
የቀድሞው የቶተንሃም እና የሪያል ማድሪድ ኮከብ በዌልስ ብሄራዊ ቡድን 16 ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን÷ 111 ጨዋታዎችን አድርጎ 41 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.