Fana: At a Speed of Life!

የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ጋር ተወያዩ፡፡

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ በሆኑት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ መሪነት የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር በጽህፈት ቤታቸው በመገኘት በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በአውሮፖ የአሜሪካ ዋና ዳይሬክተር እና በሊጉ የዋና ፀኃፊው የዶክተር ሙሐመድ አብዱል ከሪም አልጊሳ ረዳት በሆኑት በዶክተር አብዱል አዚዝ ሰርሃን የተመራውን ልዑክ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ ለሆኑት ለሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ባቀረበዉ ጥያቄ መሰረት ዉይይት አድርገዋል።

በውይይቱም የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ቡድን መሪ የሆኑት ዶክተር አብዱል አዚዝ ሰርሃን በኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና ለህብረተሰቡ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

ውይይቱ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር በሰላምና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.